በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ችግሮች ሲያጋጥሙ የሚፈቱበት ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቶች አሉ::
ከእነዚህ መካከል አንዱ በሃዲያዎች ምድር የተጣላ የሚታረቅበት የባህላዊ ደኝነት ስርዓት “ለምቤ ዳና” ይባላል::
በለምቤ ዳና ባህላዊ ዳኝነት ከስድስት እስከ ስምንት ዳኞች ይሰየማሉ፤ የቁጥሩ ሁኔታ የሚወሰነው ለዳኝነት እንደ ቀረበው ጉዳይ ይሆናል።
ታዲያ በለምቤ ዳና ባህላዊ ዳኝነት የተሰጠው ወሳኔ ከመሬት ጠብ አይልም ሲሉ የዘጠና ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ የሃዲያ አባገዳ እና የባህላዊ ዳኛ አዲሴ መንደጎ ከኤ ኤም ኤን ዲጅታል ጋር ባደረጉት ቆይታ ነግረውናል።
ዕርቅ እና ዳኝነት ከግለሰብ እስከ ማህበረሰብ አልፎም ለሃገር ያስፈልጋል፣ ስለሆነም ይህንን ባህል ጠብቆ ለማቆየት ወጣቱ ሃላፊነት አለበት ነው ያሉት።
አሁን ላይ እንደ ሃገር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ለማክበር መመረጣችን ባህልና እሴቶቻችን እንድናስተዋውቅና እርስ በእርስ እንድንተዋወቅ ዕድል የሚፈጥር አጋጠሚ ነው፤ እንግዶቻችን ለመቀበልም ዝግጁ ነን ብለዋል::
ኢትዮጵያዊን አንድ ሆነን ሕዳሴ ግድብን እንዳጠናቀቅው ሁሉ በቀጣይም ለሃገራችን ሰላም እና ልማት በጋራ እንቁም ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በያለው ጌታነህ