በጎነት ለወንድማማችነት

You are currently viewing በጎነት ለወንድማማችነት

AMN – ህዳር 26/2018 ዓ.ም

“ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 2ዐኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ከቀናት በኋላ ይከበራል።

በየዓመቱ የሚከበረው ይህ በዓል የአንድነትና የአብሮነት መገለጫና ማስተሳሰሪያ መድረክ ነው።

የሃድያ ወጣቶችም በበዓሉ ለመታዳም ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች በቆይታቸው ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው እና ከተማቸውን ለማስተዋቅ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

እነዚህ የበጎ ፈቃደኛና የሰላም ሰራዊት የሆኑት ወጣቶች፣ በከተማዋ ጎዳናዎች ሰንደቅ ዓላማ በመስቀልና የእንግዶች መቀበያ ቦታዎችን ዝግጅት እያስተባበሩ ይገኛሉ፡፡

ወጣት ራሔል ሄርሱሞ በጐ ፍቃደኛ ስትሆን ለሚመጡ እንግዶች ከተማዋን ለማስተዋወቅ እና ባህልና እሴቶቿን ለማጋራት ዝግጁ ነኝ ስትል ለኤ ኤም ኤን ዲጅታል ሃሳቧን አካፍላናለች::

ሌላኛው ወጣት ኤልሳ ካሱ ይባላል፤ በዓሉ የተለያዩ የብሄር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህልና እሴት ለማወቅ ዕድል እንደሚፈጥርለት ነግሮናል።

እኛ ኢትዮጵያዊያን የብዙ ባህልና እሴት ባለቤት ነን፤ ስለሆነም ይህ ልዩ ፀጋ በከተማችን መዘጋጀቱ ከሌሎች አከባቢ ከሚመጡ ወጣቶች ጋር እንድንተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚ በመሆኑ በቆይታቸው ጥሩ ትዝታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ከጓደኞቼ ጋር በመሆን የበጐ ፍቃድ ስራ ላይ እገኛለሁ ነው ያለን።

ሌሎች በበጐ ፍቃድ የተሰማሩ ወጣቶችም ከተማዋን በማስዋብ እና ሌሎች ተግባራትን በማከናወን እንግዶቻቸውን ለመቀበል ዝግጁ ሆነናል ሲል ነው አስተያየታቸውን ያካፈሉን።

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review