አዲስ አበባ ከተማ የሰላም እሴት ቁንጮና ተምሳሌት እንድትሆን ተማሪዎች እና መምህራን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

You are currently viewing አዲስ አበባ ከተማ የሰላም እሴት ቁንጮና ተምሳሌት እንድትሆን ተማሪዎች እና መምህራን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

AMN ታኅሣሥ 11/2018

አዲስ አበባ ከተማ የሰላም እሴት ቁንጮና ተምሳሌት እንድትሆን ተማሪዎች እና መምህራን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የአዲስ አበባ ሰለምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጠየቀ::

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በሴኩላሪዝም አተገባበርና የሰላም ግንባታ ትግበራን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄዱ ነው ::

ተማሪዎችና መምህራን የሰላም ፣ የፀጥታና ከፍ ሲል በአብሮነትና በመከባበር ሀገራዊ ኃሊፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ስንቅ የሚያዝበት መድረክ መሆኑን ያነሱት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በከተማዋ የተጀመሩ የሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ አዲስ አበባ ከተማ የሰላም እሴት ቁንጮና ተምሳሌት እንድትሆን ተማሪዎች እና መምህራን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በተለይም በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥና አካባቢ ያሉ አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጸሙ ግለሰቦችን በመከላከልና በማስተማር የትምህርት ማህበረሰቡ ሀላፊነት መሆኑንም አንስተዋል።

በየትምህርት ተቋማት የሚገኙ የሰላም ክበባት እንዲጠናከሩና የሰላም አምባሳደር እንዲሆኑ ሁለቱ ቢሮዎች በትብብር ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊና ትክክለኛ ሀገር ተረካቢ ዜጎች የሚፈጠሩበት እንዲሆን ማስቻል የመድረኩ ሌላኛው ዓላማ ስለመሆኑም ለመረዳት ተችሏል።

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review