ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬት የኤሌክትሪክ እና የኢንተርኔት ተደራሽነት አስቻይ መሠረቶች ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬት የኤሌክትሪክ እና የኢንተርኔት ተደራሽነት አስቻይ መሠረቶች ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

‎AMN ታኅሣሥ 12/2018 ዓ.ም

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ብሔራዊ ስትራቴጂ ግቦቹን እንዲመታ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢንተርኔት ትስስር መሠረታዊ አስቻይ ጉዳዮች መሆናቸውን ገለጹ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለዲጂታል ሽግግር ስኬት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን እንደ “ቴክኖሎጂ ምግብ” እንደሚቆጠር ጠቁመዋል።

‎ማንኛውም የቴክኖሎጂ መሣሪያ ያለ ኃይል ሊሠራ እንደማይችል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሁሉም አማራጮች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ማስፋት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አሳስበዋል።

‎ በአሁኑ ወቅት በርካታ ከተሞች የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ግን ይህንን ትስስር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም እነዚህን መሠረተ ልማቶች በማሟላት ለሁሉም ዜጎች እኩል ዕድል መፍጠር እንደሚቻል በጽኑ አምኖ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review