ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ የተሽከርካሪ መንገድ መዝጋትን ታሪክ ያደረገች ከተማ

You are currently viewing ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ የተሽከርካሪ መንገድ መዝጋትን ታሪክ ያደረገች ከተማ

‎AMN – ታኅሣሥ 12/2018 ዓ.ም

‎አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹና ተስማሚ እየሆነች ትገኛለች።

‎ከዚህ ቀደም የከተማዋ ጎዳናዎች ለእግረኛም ሆነ ለተሽከርካሪ ምቹ ባለመሆናቸው፣ እግረኛውና ተሽከርካሪው እኩል የሚጋፉባቸውና ለአደጋ የተጋለጡ ነበሩ።

‎በተለይም በየመንደሩ የሚኖሩ ታዳጊዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት አማራጭ ቦታ በማጣታቸው፣ ኳስ ለመጫወት የተሽከርካሪ መንገዶችን ለመጠቀም ይገደዱ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሮ ታሪክ ሆኖ አልፏል።

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ለታዳጊዎች፣ ለወጣቶችና ለሕፃናት ምቹ የሆነች ከተማን ለመገንባት በወሰነው መሠረት ዘመን ተሻጋሪ የልማት ሥራዎችን አከናውኗል።

‎ በዚህም የከተማዋ ጎዳናዎች ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተስማሚ በሆነ መልኩ እንዲገነቡ ተደርገዋል።

‎በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች የራሳቸው የሆነ የእግረኛና የሳይክል መስመር ተሰርቶላቸው፣ በአረንጓዴ ልማትና በአበቦች አጊጠው ለእግር ጉዞ እና ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እጅግ ምቹ ሆነዋል።

‎በእነዚህ የታደሱና አዳዲስ ጎዳናዎች ላይ ወጣቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያንና ጎልማሶች በነፃነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መመልከት አሁን ላይ የተለመደ የከተማዋ ባህል ሆኗል።

‎ምቹ፣ ንፁህ፣ ጤናማና ለሁሉ ተስማሚ ከተማ!

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review