ሰባት ስኬታማ የድርጅት መሪዎች ተሸላሚ ሆኑ

You are currently viewing ሰባት ስኬታማ የድርጅት መሪዎች ተሸላሚ ሆኑ

AMN – ታኅሣሥ 12/2018 ዓ.ም

በ20ኛው የግራንድ አፍሪካ የተቋማትና የአመራር ሽልማት መርሐ-ግብር ላይ ሰባት ስኬታማ የድርጅት መሪዎች ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው መርሐ ግብር ላይ ተሸላሚ ሆነዋል።

በዚህም የቲ ኬ ትሬዲንግ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ሼኽ ቶፊቅ ከድር፣ የሰንሻይን ኮንስትራክሽን መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ፣ የሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ለማ ተሸላሚ ሆነዋል።

በተጨማሪም የኢሊሌ ሆቴል ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ፣ የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ በላይነህ ክንዴ፣ የኤ ኤም ጂ ግሩፕ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልሀኪም መሐመድ እና የቀርጫንሼ ትሬዲንግ ፒ ኤል ሲ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል ደገፋ ተሸልመዋል።

ድርጅቱ የሥራ መሪዎቹን የሸለመበት ምክንያት ከሀገር አልፎ በአሕጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ባሳዩት የላቀ የአመራርነት ብቃት መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review