ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ እና በብሔራዊ ጉዳይ ላይ ዘመኑን የሚመጥን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባቸዋል

You are currently viewing ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ እና በብሔራዊ ጉዳይ ላይ ዘመኑን የሚመጥን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባቸዋል

AMN- ታኅሣሥ 13/2018 ዓ.ም

ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ እና በብሔራዊ ጉዳይ ላይ ዘመኑን የሚመጥን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው ከሸገር ሲቲ፣ ከሐረሪ ክልል እና ከተማዋ ወጣቶች ጋር “በሰላም እሴት ግንባታ የወጣቶች ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እያካሄደ ነው።

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ እና በብሔራዊ ጉዳይ ላይ ዘመኑ የሚመጥን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው ገልጸዋል ።

በጋራ መቆም የሚያስችል ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አስተሳሰብ ማዳበር እንደሚገባም ኃላፊው ተናግረዋል።

የወጣቶችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ ለማረጋገጥ ሰላም ወሳኝ ሚና አለው ሲሉም ገልጸዋል።

የውይይቱ ተሳትፎ ወጣቶችም፣ እኛ ወጣቶች የሀገር ምሰሶ ነን፣ በመሆኑንም ለሰላም ግንባታ እና አብሮነት ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review