አዲሰ አበባ ከተማ በቱሪዝም ኮንፈረስ እያሰመዘገበች ያለው ከፍተኛ መነቃቃትና ዕድገት ይበልጥ ተመራጭና የስበት ማከል እንድትሆን አድርጓታል

You are currently viewing አዲሰ አበባ ከተማ በቱሪዝም ኮንፈረስ እያሰመዘገበች ያለው ከፍተኛ መነቃቃትና ዕድገት ይበልጥ ተመራጭና የስበት ማከል እንድትሆን አድርጓታል

‎AMN ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም

‎ለጉብኝት፣ ለቆይታና ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተመራጭ ውብ ከተማ የሆነችው አዲሲቷ የአፍሪካ የዕድገት መልክ በቱሪዝም ኮንፈረስ እያሰመዘገበች ያለው ከፍተኛ መነቃቃትና ዕድገት ይበልጥ ተመራጭ፣ የስበት ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል።

‎በተለይም፣ የቱሪዝም ኮንፍረንስ መስሕብነት የሚያሳድጉ ደረጃቸውን የጠበቁ ኮንቬንሽን ማዕከላት፣ የወንዝ ዳርቻ መሠረተ-ልማቶች፣ ሁሉን-አቀፍ ፓርኮች ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ሙዝየሞች ፣ ምቹ መንገዶች ፣ የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎች እና ሞተር አልባ የትራንስፖርት አማራጭን ጨምሮ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ እና ደረጃቸውን የጠበቁ ፕላዛዎች ለጉብኝት እና ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተማራጭ ከተማ እንድትሆን አስችሏታል፡፡

Processed with VSCO with c1pro preset

‎በተጨማሪም ሀገር በቀል እጽዋት መገኛ የሆነው ጉለሌ እጽዋት ማዕከልን ጨምሮ በከተማዋ ዙሪያ የከበቡ ታሪካዊ ዋሻዎችና ቅርሶች የጎብኚዎችን ቀልብ እንዲያርፍባት አድርጓል፡፡

‎በሌላ በኩል በመዲናዋ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው የጉላ ሰው ተኮር ልማቶች በአለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ በቀዳሚነት ስሟ እንዲጠቀስ አድርጓል፡፡

‎አዲስ አበባ በፍጥነት እያስመዘገበች በምትገኘው አስደማሚ ለውጦች፣ በርካታ አለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ሁነቶችን እና ኮንፍረንሶችን በማዘጋጀት ተወዳዳሪ ከተማ መሆኗን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review