አዲስ አበባ ውስጥ በሔዱበት ሁሉ አረፍ የሚሉበት ሥፍራ አለ

You are currently viewing አዲስ አበባ ውስጥ በሔዱበት ሁሉ አረፍ የሚሉበት ሥፍራ አለ

AMN – ጥር 5/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ በሄዱበት ሁሉ ሕፃናት የሚጫወቱበት፣ ሻይ ቡና የሚጠጣበት፣ የሚበላበት እና አረፍ የሚባልበት ሥፍራ መኖሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የአዲስ አበባ ወንዞች ትንሣኤ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የዘጋቢ ፊልም ላይ በመዲናዋ የተከናወኑ የወንዝ ዳርቻ እና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በተመለከተ ጉብኝት እና ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻቸውም ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ማድረግ ማለት ከብክለት ነጻ የሆነችና አረንጓዴ ከተማ ውስጥ የተለያዩ መገልገያ ቦታዎችን ማለትም ማረፊያ፣ መዝናኛ፣ መነገጃ፣ የሥራ ዕድል ማግኛ፣ መብያ፣ መጠጫ እና በጋራ በፍቅር የሚኖርበት አካባቢ ማድረግ መሆኑን ነው ከንቲባ አዳነች ያስረዱት፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review