የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዘርፉ የጎላ ሚና ያላቸው ቁልፍ ተቋማትን ወልዷል ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ገለጹ

You are currently viewing የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዘርፉ የጎላ ሚና ያላቸው ቁልፍ ተቋማትን ወልዷል ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ገለጹ
  • Post category:ኢኮኖሚ

AMN ጥር 9/2018

የለውጡ መንግሥት ያከናወነው የኢኮኖሚ ሪፎርም በኢኮኖሚ ረገድ ቁልፍ ሚና ያላቸው ተቋማት መውለዱንና የኢኮኖሚ ዕድገቱንም ማቃናቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ”የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ ” በሚል ሐሳብ በተካሄደ ኮንፈረንስ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻቸውም፤ከሰባት ዓመታት በፊት ኢኮኖሚውን የገጠሙት ዋና ዋና የማክሮ ፊሲካል ተግዳሮቶችን አንስተዋል።

እነዚህ ተግዳሮቶችም፤ ከፍተኛ የዋጋ ንረት፣ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት፣ ዘላቂና አስተማማኝ የፊሲካል ቁመና አለመኖር፣ ከፍተኛ የዕዳ ጫና፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እና የገበያ አለመረጋጋት መሆናቸውን አብራርተዋል።

ስለዚህ ይህን የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራት ለመጠገን ላለፉት ሰባት ዓመታት መንግሥት፤ በመጀመሪያው እና በሁለተኛው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ሊከሰት የነበረውን የማክሮ ፋይናንሻል ቀውስ አስቀርቷል ብለዋል።

በዚህም ጠንካራ ዕድገትን አስመዝግቦ በሁሉም የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች (ኢንዲኬተሮች) ወደ ተሻለ ቁመና ለመሻገር ተችሏል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት አንዷ ልትሆን ትችላለች ነው ያሉት።

የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ጠንካራ ተቋማት የተፈጠሩበት መሆኑን በአጽንኦት ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ስለዚህ ከተቋማት ግንባታ አንጻርም በኢኮኖሚ ረገድ ቁልፍ ሚና ያላቸው ተቋማትን የወለደ ሪፎርም ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የኢኮኖሚ ዕድገቱን ያቃና ሪፎርም መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህም በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review