ኢትዮጵያ በዘንድሮዉ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ እያደረገች ያለዉ ተሳትፎ ሃገሪቱ ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ እድገትን ለማምጣት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በዘንድሮዉ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ እያደረገች ያለዉ ተሳትፎ ሃገሪቱ ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ እድገትን ለማምጣት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ

AMN-ጥር 14/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በዘንድሮዉ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ እያደረገች ያለዉ ተሳትፎ ሃገሪቱ ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ እድገትን ለማምጣት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ፣ አራተኛ ቀኑን በያዘው የ2026 የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም (World Economic Forum) ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የዓለም አቀፍ ጤና እና ፋይናንስ የወደፊት ዕጣ ፈንታን አስመልክቶ በቢል ጌትስ አስተናጋጅነት ትላንት በተካሄደው ዉይይት ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በመጠቀም፣ በተለይም በገጠሪቱ የአገሪቱ ክፍሎች የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት እያደረገች ያለውን እድገት አብራርተዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የጤና ስርአቶችን ለማጠናከር፣ የሰዉ ሃይል ልማትን ለማበረታታት እና የዲጂታል መሰረተ ልማትን ለማሳደግ የረጅም ጊዜ አጋርነት እና ዘላቂ ፋይናንስ እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ “ከድንገተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ባሻገር ያሉ ኢኮኖሚዎች” በሚለው የውይይት መድረክ ላይም ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት ለመገንባት የሚያስፈልጉ ቁልፍ አምዶችን ዘርዝረዋል፡፡

አቶ አህመድ ሽዴ ከፎረሙ ጎን ለጎን ከቢል ጌትስ እና ከአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ይህም ኢትዮጵያ ለፈጠራ፣ ለአጋርነት እና ለዘላቂ ልማት ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ያረጋገጠ ነው።

እስካሁን ያለው የኢትዮጵያ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም 2026 ተሳትፎ፣ አገሪቱ ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ እድገትን ለማምጣት ፈጠራን፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እና ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ለመጠቀም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገንዘብ ሚኒስቴር ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review