የባሕርዳር አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የባሕርዳር አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN- ጥር 16/2018 ዓ.ም

የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ እና በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱን ተርሚናል ጎብኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ተርሚናሉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ፣ ለተሳፋሪዎች ተመቻችቶ፤ ለዕይታ ተስማምቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርብ ወራት ውስጥም ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review