የዘንድሮ ምርጫ ባለፈው ካየነው ምርጫ በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክረን እየሰራን ነው :- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

You are currently viewing የዘንድሮ ምርጫ ባለፈው ካየነው ምርጫ በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክረን እየሰራን ነው :- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
  • Post category:ፖለቲካ

AMN-ጥር 27/2018 ዓ.ም

የዘንድሮ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሃዊ አካታች ባለፈው ካየነው ምርጫም በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ትናንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ መንግሥት በዘንድሮ ምርጫ ዙሪያ እየሰራ ያለውን ተግባር ጠቅሰዋል፡፡

ምርጫው ባለፈው ከነበረው ምርጫ የተሸለ አሳታፊ እንዲሆን መንግሥት አቋም ይዞ እየሰራ እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

ከምርጫ ጋር የሚነሱ ችግሮችን ለመፈተሸ ሚኒስትሮች ሁሉም በሚባል ደረጃ በክልሎች እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

የተሻለ ምርጫ ይኖራል የሚል እምነት አለኝ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ አሁን ያለው ፓርላማ ካሉት አምስት እና አስር ሰዎች በአስር እጥፍ ያደጉ ድምጾች ይሰሙበታል የምል እምነትና ፍላጎትም እዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱ የአንድ ፓርቲ ድምጽ ከሆነ ለኢትዮጵያ አይጠቅማትም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

መንግስት ምርጫውን በሚመለከት እያደረገ ያለው ስልጠና እና ክትትል ብዝሃ ድምጽ እንዲሰማበት ማስቻል እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

መንግስት አውድ ከማስፋት አንጻር ብቻ ሳይሆን ይሁነኝ ብሎ ይሰራበታልም ብለዋል፡፡

ሚዲያዎች ለፓርቲዎች ዕድል አይሰጡም በሚል ለተነሳው ጥያቄም በቂ ዝግጅት መኖሩን ጠቁመው፣ ምክር ቤቱ የሚቀር ካለ ጠርቶ አቅጣጫ መስጠት እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡

ሚዲያዎች ለሁሉም በሚገባው ፣ በህግ አግባብ ማገልገል አለበት ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review