ዛሬ “ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትጽና” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና አሻራ በተቀመጠበት ገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከመላ ከተማችን ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም አካሂደናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ስለ ወጣቱ ተጠቃሚነት ችግርን እያወራን ሳይሆን 24/7 እየሰራን ለችግሩ ተግባራዊ ምላሽ ከሰጠንባቸው እና ተጠቃሚነቱን ካረጋገጥንባቸው ስፍራዎች አንዱ በሆነው በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ70 ሺህ በላይ ከሆኑ የከተማችን ወጣቶች ጋር በስፓርታዊ እንቅስቃሴ የምርጫ ቅስቀሳ አድርገናል።

ባለፉት 5 ዓመታት የሰራናቸው የልማት አሻራዎች የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት ይመሰክራሉ። ከማንም በላይ ሀገር እየተገነባች ያለችው ለወጣቶቻችን በመሆኑ የብልፅግናዋ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ።

የከተማችን ወጣቶች የፓርቲያችንን ራዕይና የወደፊት አሻራ ሁለንተናዊ እድገት ሰንቃችሁ፥ ተስፋ ተጋርታችሁ ማልዳችሁ ከአራቱም አቅጣጫዎች በመትመም ድጋፋቸሁን ስለገለፃችሁልን በራሴ እና በፓርቲዬ ብልፅግና ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

መንገዳችን መደመር፤ መዳረሻችን ብልፅግና ነው!

ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር !

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review