የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በትምህርትና በጤና ዘርፎች የለውጥ አብዮት አካሂዷል – አቶ ጃንጥራር አባይ

You are currently viewing የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በትምህርትና በጤና ዘርፎች የለውጥ አብዮት አካሂዷል – አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN- ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ዓመታት በትምህርትና በጤናው ዘርፍ የለውጥ አብዮት ማካሄዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ።

ምክትል ከንቲባው ይህንን የገለጹት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ባበቁበት ወቅት ነው።

የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አምስት ዓመታት ያለምንም እረፍት ስኬታማ የልማት ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን የገለጹት አቶ ጃንጥራር፤ በተለይም በትምህርት ዘርፍ በተሠሩ ዘመናዊ ሥራዎች ሕፃናት ከልጅነታቸው ጀምሮ ብሩህ አእምሮ ኖሯቸው እንዲያድጉና ለሀገር ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል።

በጤናው ዘርፍም ቢሆን እንደ ከተማ በተከናወኑ ተግባራት አዳዲስ ጤና ጣቢያዎችን በመገንባትና የነበሩትን አቅም ከማሳደግ ባለፈ፣ ሆስፒታሎች ደረጃቸውን ጠብቀው ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ገልጸዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በክፍለ ከተማው በተለያዩ ወረዳዎች ተገንብተው ዛሬ የተመረቁት 8 የልማት ፕሮጀክቶች ከ420 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

የቄርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችም ዛሬ የተመረቁት የልማት ስራዎች ችግር ፈችና የህዝቡን ጥያቄ የመለሱ ናቸው ብለዋል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review