ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተሳካ ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ እንዲሆን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

You are currently viewing ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተሳካ ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ እንዲሆን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ጥር 28/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ6 ወር አፈጻጸሙን ገምግሟል።

የጋራ ምክር ቤቱ ባለፈው ግማሽ ዓመት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቅም ለማጎልበት ሲሰሠራ ስለመቆየቱም ተነስቷል።

በብሔራዊ ጥቅም ላይ እንደ ሀገር ለመስራት ተግቶ እየሰራ ስለመሆኑም የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ወይዘሮ አዲስ መሐመድ ገልጸዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በ2014 ዓ.ም. የተቋቋመ ነው ያሉት ሰብሳቢዋ በዚህ አጭር ጊዜም ሀገራዊ በሆኑ በማኅበራዊና በጎ ፈቃድ ሥራዎች ሲሳተፍ እንደቆየም ገልጸዋል።

ቀጣይ የሚከናወነው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተሳካ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ እንዲሆን እየተሠራ ነውም ብለዋል ሰብሳቢዋ።

በጽዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review