በከተማ አስተዳደሩ በ”ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ ከ2.23 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በከተማ አስተዳደሩ በ”ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ ከ2.23 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ጥር 29 ፣ 2018

“ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል ያስቻለ የኅብረተሰብ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሔደ ይገኛል፡፡

ከንቲባ አዳነች የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ለከተማዉ ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

የከተማዋ ባለሀብቶች፣ ነዋሪዎች፣ የቀድሞ ተማሪዎች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በንቅናቄው የጎላ ተሳትፎ ማድረጋቸው ነው ከንቲባዋ የገለጹት ፡፡

ኅብረተሰቡ በጥሬ ገንዘብ፣ በዓይነት፣ በጉልበት እና በዕውቀት 1.32 ቢሊየን ብር ሀብት ለመሰብሰብ ታቅዶ 2.23 ቢሊየን ብር ማሰባሰብ መቻሉን ነው ከንቲባዋ የተናገሩት፡፡

የተሰበሰበውን ሀብት በመጠቀም የት/ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ለመማር ማስተማር ሒደቱ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደተቻለ ነው ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያብራሩት፡፡

የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ ቀሪ ተግባራትን ማከናወንና ጅምሮቹን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review