AMN – የካቲት 6/2018 ዓ.ም.
ሁለተኛው የአፍሪካ ጣሊያን ጉባዔ ዛሬ በመዲናችን አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሔዳል።
ጉባዔው የአፍሪካንና የጣሊያንን ግንኙነት አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብሮችን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፡፡
በጉባኤው ላይ በርካታ ተሳታፊዎች የሚገኙ ሲሆን ይህም አዲስ አበባ ከተማ ታላላቅ ጉባዔዎችን የማስተናገድ አቅሟን የሚያሳይ ይሆናል፡፡
የመጀመሪያው የአፍሪካ ጣሊያን ጉባዔ በጣሊያን ሮም የተካሄደ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአዲስ አበባ ይካሔዳል።
ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እና የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔን ለማስተናገድ ተዘጋጅታ እንግዶቿ በመቀበል ላይ ናት፡፡
በአስማረ መኮንን