ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረገችው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ ምስጋና ይገባታል- ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረገችው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ ምስጋና ይገባታል- ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ

AMN የካቲት 8/2018

ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረገችው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ ምስጋና ይገባታል ሲሉ የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ-መንበርና የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ገለጹ፡፡

39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተያዙለትን አጀንዳዎች በስኬት በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን አግኝቷል።

የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ-መንበርና የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አባል ሀገራቱ ለጉባኤው መሳካት ላበረከቱት የጋራ ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በአጀንዳው ላይ የተያዙት ነጥቦች በስኬት በመጠናቀቃቸው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በይፋ መጠናቀቁን አሳውቃለው ብለዋል።

ሊቀ-መንበሩ ኢትዮጵያ ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅና ልዑካኑም ምቹ ቆይታ እንዲኖራቸው ላደረገችው አስተዋጽኦ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ውብ በሆነችው የአህጉራችን መዲና አዲስ አበባ ተቀብላ ላስተናገደችን ኢትዮጵያ ምስጋናዬ የላቀ ነው ሲሉ መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መሪዎቹና ልዑካናቸው ወደ የሀገራቸው የሚያደርጉት ጉዞ የሰላም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review