ኢትዮጵያ የመልክዓ ምድር እስረኛ ሆኗ መቆየቷ አግባብነት ስለሌለዉ የባህር በር ጉዳይን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የቱርክዬ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ ሚናዉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የመልክዓ ምድር እስረኛ ሆኗ መቆየቷ አግባብነት ስለሌለዉ የባህር በር ጉዳይን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የቱርክዬ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ ሚናዉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

AMN የካቲት 10/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የመልክዓ ምድር እስረኛ ሆኗ መቆየቷ አግባብነት ስለሌለዉ የባህር በር ጉዳይን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የቱርክዬ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ ሚናዉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በብሔራዊ ቤተመንግሥት የጋራ መግለጫ ሰጥዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመግጫቸዉ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ጥቂት ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗን እና በዚህ አመት የ10.2 በመቶ እድገት ልታስመዘግብ እንደምትችል ገልጸዋል፡፡

የእድገቱ ቀጣይነት መረጋገጥ የሚችለዉ ግን ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሃገር የባህር በር ሲኖራት ብቻ ነዉ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በጠላቶች ደባ በአለም ላይ ካለዉ ነባራዊ ሁኔታ እና እዉነታ ዉጪ የባህር በር እንድታጣና በቀጠናዉ የመልክዓ ምድር እስረኛ ሆኗ እንድትቆይ መደረጉ አግባብነት የሌለዉ መሆኑን በጥልቀት መምከራቸዉን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ የተነሳም እንደ ቱርክዬ ያሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሃገራት በዲፕሎማሲዉ መስክ ጫና በመፍጠር ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ማግኘት የምትችልበት ሁኔታ እንዲያግዙ በስፋት መወያየታቸዉንም ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ የበኩላቸዉን ሚና እንዲጫወቱ ጠንካራ ዉይይት መደረጉንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመግለጫቸዉ አንስተዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review