ስኬታማ በሆነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላገኛችሁት ውጤት እንኳን ደስ ያላችሁ – የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም

You are currently viewing ስኬታማ በሆነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላገኛችሁት ውጤት እንኳን ደስ ያላችሁ – የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም

AMN ሰኔ 16/2018

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም 7ተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ላሸነፈው ብልጽግና ፓርቲ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት በመጥቀስም በወቅቱ በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና በውይይቱ ላይ በተነሱ ትርጉም ያላቸው ሀሳቦች መደሰታቸውንም አስታውስዋል።

እርሳቸውና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዓለም አቀፋዊ ሁነቶች ያላቸው ምልክታ ተመሳሳይ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፣ የደቡብ ንፍቀ ክበብ (Global South) አገራት በእኩልነትና በትብብር በመስራት ረገድ ትልቅ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ማሌዥያ ከአፍሪካ ጋር ባላት ግንኙነት ውስጥ ኢትዮጵያ ታላቅ ስፍራ እንዳላት ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ባለፈው ዓመት የተጀመሩ በርካታ ሥራዎችን በጋራ ወደፊት ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሒም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለብልጽግና ፓርቲ በጠቅላላ ምርጫው ላስመዘገቡት ድል እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review