“አርሰናል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የማሸነፍ አቅም አለው” አንጅ ፖስቴኮግሉ

You are currently viewing “አርሰናል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የማሸነፍ አቅም አለው” አንጅ ፖስቴኮግሉ

AMN-የካቲት 13/2018 ዓ.ም

የቶተንሃም ሆትስፐርስ የቀድሞ አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሎ አርሰናል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት አቅም አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዋነኛነት በጋሪ ኔቭል በሚዘጋጀው ስቲክ ቱ ፉትቦል (Stick to Football) ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፖስቴኮግሉ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ለማሸነፍ አርሰናል የተሸለ እድል እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

“አርሰናል ከኢንተር ሚላን ጋር ያደረገውን የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ተመልክቼ በብቃታቸው ተደምሜያለሁ ፤ የተሟላ ስብስብ ስላላቸው አንዳንዴ ጥሩ ባይጫወቱ እንኳን የተለየ የአቋም መውረድ ይገጥማቸዋል ብዬ አልጠብቅም” ብለዋል ፖስቴኮግሉ፡፡

ማንችስተር ሲቲ ባለፉት ዓመታት የተለየ ከፍታ ላይ መድረስ እንደሚቻል አሳይቷል ያሉት የሴልቲክ የቀድሞ አሰልጣኝ ዘንድሮ ግን ያን ደረጃቸውን አላየንም ብለዋል፡፡

በውድድር ዓመቱ ወጥነት ያለው ብቃት ያሳየው አርሰናል ነው ፤ ምናልባት በአራት ውድድሮች ላይ ተፎካካሪ መሆኑ ካልጎዳው በስተቀር የሊጉን ዋንጫ የማሸነፍ አቅም እንዳለው አውስትራሊያዊው አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ መስክረዋል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review