AMN – የካቲት 18/2018 ዓ.ም
ዛሬ ማለዳ ለእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን እና ለሀገር ሉአላዊነት ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች ታሪክን አስጎብኝተናቸዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለነበራቸው ጊዜ እያመሰገንን፤ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ እመኛለሁ ብለዋል።