አዲስ አበባ ተመራጭ የቱሪዝም ማዕከል እየሆነች ነው – ሚስተር ሺራዝ ሐሰን

AMN ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ. ም

በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እንዲሁም የቱሪዝም መሠረተ ልማቶች ከተማዋ ተመራጭ የቱሪዝም ማዕከል እየሆነች ስለመምጣቷ ማረጋገጫ መሆኑን የፋሜ ባይ ሺራዝ መስራች ሚስተር ሺራዝ ሐሰን ገለጹ፡፡

የፋሜ ባይ ሺራዝ “FAME by Sheeraz” መስራች ሚስተር ሺራዝ ሐሰን እና ልዑካን ቡድናቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እና የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶችን የጎበኙ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እንዲሁም የቱሪዝም መሠረተ ልማቶች ከተማዋ ተመራጭ የቱሪዝም ማዕከል እየሆነች ስለመምጣቷ ማረጋገጫ ነው ሲሉ ልዑካኑ ተናግረዋል::

ፋሜ ባይ ሺራዝ ስመጥር የዲጂታል ሚዲያ እና የብራንዲንግ ድርጅት ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ግለሰቦችን እና ተቋማት ጋር በቅርበት የሚሰራ ተቋም መሆኑን ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review