AMN- የካቲት 28/2018 ዓ.ም
ለ2ኛ ጊዜ የሚከናወነው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዓመታዊ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ዛሬ ተጀመሯል።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋን ጨምሮ የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት እና ሰራተኞች በተገኙበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተከናውኗል።
በሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበረው የመክፈቻ ስነ ስርዓት በአመራሮች መካከል አዝናኝ የእግርኳስ ጨዋታ ተከናውኗል።
ስፖርታዊ ፌስቲቫሉ የአንድነት ስሜት ፣ ፍቅርን እና የስራ ተነሳሽነት ስለሚፈጥር ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን አቶ ካሳሁን ተናግረዋል።
ፌስቲቫሉ ጠቀሜታው የጎላ ስለሆነ በዓመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ ሊከናወን እንደሚገባም ጠቁመዋል። ለዚህም የተቋሙ አመራርም አስፈላጊውን ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በከተማዋ ስፖርታዊ ሁነቶችን ለማከናወን ምቹ ቦታዎች ተፈጥረዋል ያሉት ዋና ስራአስፈፃሚው ይህን ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋለ።
2ኛው ዓመታዊ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሰራተኞች ስፖርታዊ ፌስቲቫል በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ለሳምንታት መከናወኑን ይቀጥላል።
በሸዋንግዛው ግርማ