AMN የካቲት 29/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርቶች እና አገልግሎቶች ጥራት የማረጋገጥ ስራ ዓለም አቀፍ አሰራር ስርዓትን መሰረት በማድረግ ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች፣ ለተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቶች፣ ለምርምር ተቋማት እና በአጠቃላይ ለሸማቹ ማህበረሰብ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎትን የሚሠጥ መንግስታዊ ድርጅት ነው ብለዋል፡፡

በድሬዳዋ አካባቢ ለሚገኙ አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ነፃ የንግድ ቀጣና እንዲሁም የደረቅ ወደብን መሰረት በማድረግ ቀደም ብሎ ይሰጡ ከነበሩ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች በተጨማሪ በምግብ ዘይት፣ ፔትሮሊዬም ወይም የነዳጅ ምርት፣ የተለያዩ የምግብ ምርቶች፣ የማስዋቢያና የዲተርጀንት ምርቶች፣ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ምርቶችንና ግብዓቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አዲስ የፍተሻ ላቦራቶሪ በማደራጀት አገልግሎቱን ተደራሽ አድርጓል ሲሉ ገልጸዋል፡፡