የኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ ለመምከር መሰባሰብ ብስለታቸውንና አርቆ አሳቢነታቸውን ያሳየ ነው

You are currently viewing የኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ ለመምከር መሰባሰብ ብስለታቸውንና አርቆ አሳቢነታቸውን ያሳየ ነው

AMN ሐምሌ 7/2018

ኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ ንግግር እና በሰላማዊ ውይይት ለመምከር መሰባሰባቸው ብስለታቸውንና አርቆ አሳቢነታቸውን ያሳየ ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ገለጹ።

ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት እኛ ኢትዮጵያዊያን የስልጣኔ አብነት፣ የአብሮነት ምልክት፣ የነፃነት ፋና፣ የጥበብ ጀማሪ እና ባለብዙ ፀጋ ነን ብለዋል።

በመሆኑም ይህን እንደ ሀገር የመመካከር ዕድል በተገቢው ተጠቅሞ ልዩነታችንን በስልጡን ምክክር መፍትሄ በመስጠት ታሪክ ሰርቶ ማለፍ አሁን ላለነው ትውልድ ትልቅ እና አይረሴ ድል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በአንድም ሆነ በሌላ በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠሩና ለአብሮነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ ለመፍታት አሁን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱና በሀገር አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ስለኢትዮጵያ በሰለጠነ ንግግር እና በሰላማዊ ውይይት ለመምከር መሰባሰባቸው የሀገሬን ልጆች ብስለት፣ አርቆ አሳቢነት እንዲሁም የኢትዮጵያንም ከፍታ እና የወደፊት ብሩህ ተስፋ ያሳየን ነው በማለት በምክክሩ ሂደት ላይ ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልጸዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆንም የሰላም ሚኒስትሩ የመልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review