ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሕፃን ብሌን ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት አስረከቡ፡፡

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሕፃን ብሌን ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት አስረከቡ፡፡

AMN- መጋቢት 2 /2018 ዓ.ም

በከፍተኛ የአንጎል ውስጥ ውሃ እና የአንጎል ግፊት መጨመር (ሀይድሮሴፋለስ) ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ለሆነችውሕፃን ብሌን አሸናፊ ቤተሰቦች የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት የመኖሪያ ቤት አስረክበዋል።

ባለፉት 10 ዓመታት በገጠማት ሕመም ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆና የቆየችነው ሕፃን ብሌንን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቀናት ቤቷ ድረስ ሔደው መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በጉብኝታቸው ወቅት ሁለት ሕጻናት ልጆቹን የከተማ መንገድ በማጽዳት ሥራ ላይ ተሰማርቶ እያሳደገ የሚገኘው አባታቸውን ወታት አሸናፊን ጥንካሬ በማድነቅ ሕፃኗ ወደውጭ ሀገር ተጉዛ አስፈላጊውን ሕክምና እንድታገኝ የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገውለት ነበር።

ሕፃን ብሌን የታዘዘላትን የፊዚዮቴራፒ ህክምና እንድትከታተል በአሁኑ ወቅት የሚኖሩበት ቤት የማይመችና ከሕመሟ ባሕሪ አንጻር እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ቤተሰቡ የተሻለ መኖሪያ ቤት እንዲያገኝ መወሰኑን በጎበኟት ወቅት ገልጸው ነበር፡፡

ከንቲባዋ ባዛሬው ዕለት በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ የጂ+4 የመኖሪያ ሕንጻ፣ ለማኅበራዊ ችግር ለተጋለጡ ወገኖች፣በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለሀገር ባለዉለታ ለሆኑ ነዋሪዎች ሲያስረክቡ የሕፃን ብሌን ቤተሰቦችም ቤት እንዲያገኙ አድርገዋል ሆነዋል፡፡

የሕፃን ብሌን አባት ወጣት አሸናፊ ከከንቲባ አዳነች አቤቤ እጅ የቤቱን ቁልፍ ተረክቧል፡፡

በታደሠ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review