AMN- መጋቢት 03/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ “የመደመር መንግሥት እይታ በሀይማኖት ተቋማት በሚል መርህ ከወንጌላውያን አማኞች የሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናስ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን የሀይማኖት ተቋማት የሞራልና የስነ-ምግባር እሴቶችን በትውልዱ በማስረፅ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸውን ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የሃይማኖት አባቶች ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው መሆኑን ያነሱት አቶ አብዱልቃድር ይህንን ተቀባይነት በመጠቀም ጥላቻን በመከላከልና ፍቅርን በመስበክ በትውልዱ ላይ መስራትም እንደሚገባም አስተዋል።
በውይይቱ መድረኩ የወንጌላውያን አማኞች እና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት በአራዳ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በራሄል አበበ