AMN መጋቢት 5/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መንግሥት ለተጎጂ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ እና ሌሎች ወረዳዎች በበልግ ዝናብ ምክንያት በተከሠተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ ዜጎቻችን የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ ብለዋል፡፡
መንግሥት ለተጎጂ ወገኖቻችን አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ተገቢው ጥናትና ሥራ መከናወን አለበት። የጥንቃቄ ተግባራትም አስፈላጊዎች ናቸው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡