AMN መጋቢት 07/2018
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ፣በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በህይወትና በንብረት ላይ ለደረሰዉ ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ገልጸዋል።
ሊቀመንበሩ ለተጎጂ ቤተሰቦች ልባዊ መፅናናትን የተመኙ ሲሆን በአደጋው ለተጎዱ ማህበረሰቦች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ የተረፉትን ለመታደግና ለተቸገሩት እርዳታ ለማቅረብ ሳይታክቱ እየሰሩ ለሚገኙ የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች፣ የሰብአዊ ረድኤት ባለሙያዎች እና የአካባቢው በጎ ፈቃደኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በዚህ ብሄራዊ የሀዘን ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል።
ለቀጣይ የእርዳታና መልሶ ማቋቋም ስራዎች ያለውን ድጋፍም በድጋሚ ገልጿል።