በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሃይማኖታዊ ሃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ገለጹ

You are currently viewing በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሃይማኖታዊ ሃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ገለጹ

AMN መጋቢት 8/2018 ዓ.ም

በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሃይማኖታዊ ሃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ገልጸዋል፡፡

ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የሰላምን ጉዳይ ዋንኛ አጀንዳ ሊያደርጉ እንደሚገባም ነዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የገለጹት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የሃይማኖት ተቋማት በመደመር መንግስት እይታ” በሚል መሪ ሀሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእምነት አባቶች ጋር ባካሄደዉ የዉይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ የሃይማኖት አባቶች እንደተናገሩት የሃይማኖት አባቶች ከሁሉም በላይ የሰላም ጉዳይን አጀንዳ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታየዉን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የሃይማኖት ተቋማት እና መንግስት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ የገለጹት የሃይማኖት አባቶቹ በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

ለዘመናት የቆዩና ያልተፈቱ ችግሮች ካሉም በሃገራዊ ምክክሩ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል ነዉ ያሉት፡፡

በየደረጃዉ የሚገኙ አመራሮችና የጸጥታ ተቋማት ከቤተክርስቲያኗ ጋር በትብብት በመስራታቸዉ በከተማዋ የሚካሄዱ ሃይማኖታዊ በአላት በስኬት እየተከበሩ ናቸዉ፤ ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ዉሥጥ ከሚፈጠሩ ተገቢ ካልሆኑ ሽኩቻዎች ጋር በተያያዘም ቤተ ክርስቲያን ከምትተዳደርበት ህግና ሥርዓት ባፈነገጠ መንገድ እኛ በምንላችሁ ተመሩ የሚሉ አካላት በአንዳንድ ገዳማት እና አድባራት ዉስጥ መኖራቸዉን ተሳታፊዎቹ አንስተዋል፡፡

እነዚህ አካላት ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሃገራዊ ሰላምና ልማት ስለማይበጁ ይህንን ህገ ወጥ አካሄድ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ማስተካከልና ማረም እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review