የታሪክ ክፍተትን የሞሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች – አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ቱሪስት መዳረሻ የመሆን ጉዞ

You are currently viewing የታሪክ ክፍተትን የሞሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች – አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ቱሪስት መዳረሻ የመሆን ጉዞ

AMN-መጋቢት 15/2018 ዓ.ም

“ዓድዋን የሚያህል ታሪክ ይዘን መሪዎች ወደ ሀገራችን ሲመጡ የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጡበት ቦታ አልነበረንም” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛችና የታላቅ ድል ባለቤት ብትሆንም፣ ለዘመናት የቆየውን የታሪካዊ ስፍራዎች እጥረት የዓድዋ ድል መታሰቢያ እና የታደሱት ቤተ-መንግሥታት መሙላታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቃና ቴቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሚከተሉትን ነጥቦች ዳስሰዋል፤

✅ የታሪካዊ ክፍተት መሞላት፦ የውጭ ሀገር መሪዎች ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅት በክብር የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጡበት በቂ ስፍራ አለመኖሩ ትልቅ የታሪክ ክፍተት እንደነበር ጠቁመው፣ አሁን ላይ የተገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይህንን ክፍተት በመሙላት የሀገሪቱን ገጽታ ቀይረዋል ብለዋል።

✅ ከተማን የማዘመን ራዕይ፦ አዲስ አበባ እንደ ኒውዮርክ፣ ፓሪስ እና ሪዮ ዲጄኔሮ ከተሞች የራሷ የሆኑ ዓለም አቀፍ መለያዎች (Landmarks) ሊኖሯት እንደሚገባ ገልጸዋል። በተለይ በእንጦጦ እና በየካ አካባቢ የተሰሩ ስራዎች ከተማዋን እንደ “ሆሊውድ” ያሉ ዓለም አቀፍ የቱሪስት መስህቦች ባለቤት እንደሚያደርጓት አመልክተዋል።

✅ የማንነት እና የአርበኝነት ግንባታ፦ እነዚህ የልማት ስራዎች የቱሪስት መስህብ ከመሆን ባለፈ፣ አዲሱ ትውልድ የሀገሩን ማንነት አውቆ በኢትዮጵያዊነቱ እንዲኮራና የአርበኝነት ስሜቱ እንዲገነባ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው።

ይህ ከተማን ዘመናዊ የማድረግ ስራ የኢትዮጵያ የክብር ታሪክ ለዓለም በሚመጥን መልኩ ለማሳየት ያለመ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review