AMN-መጋቢት 16/2018 ዓ.ም
የነዳጅ ስርጭትን ህጋዊ ለማድርግ በተደረገው ጥረት ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ58 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ህግ የማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮምቴ ባለፉት አራት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር ገምግሟል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በአዲስ አበባ ከተማ የህግ የበላይነትን ለማስከበርና የንግድ ስርዓቱን ለማስተካከል ሰፊ የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በእነዚህ ወራትም በተሰሩ የቁጥጥር ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውም ተገልጿል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዘይት እና ስኳር በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡
ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ ያለ ንግድ ፍቃድ በሚሰሩ እና በህገወጥ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ አስተዳዳረዊ እና ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል ተብሏል፡፡

በተለይ የነዳጅ ስርጭትን ህጋዊ ለማድርግ በተደረገው ጥረት ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ58 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር መዋሉ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
በዚህ ህገ ወጥ ድርጊት የተጠረጠሩ 35 ግለለቦች ለሕግ ቀርበዋል ተብሏል፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ