AMN- መጋቢት 17/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የአረንጓዴ ልማት ትሩፋት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ገለፀ።
ማህበራዊ እኩልነት መርህን በተከተለ መንገድ ነዋሪዎች ያለኢኮኖሚያዊ ልዩነት መዲናዋ በአረንጓዴ ልማት እያከናወነች ከምትገኘው ስራ ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ለመጪዎቹ አስር ዓመታት የምትገለገልበት የከተማ ደን ልማት ስትራቴጂ ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።
“የአዲስ አበባ ከተማ ደን ስትራቴጂ” የተሰኘው ስትራቴጂው ከተማዋ በመጪዎቹ ጊዜያት በአረንጓዴ ልማት ላይ ልትሰራቸው የሚገቡ ስራዎችን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል ስለመሆኑ ተነግሮለታል።

ስትራቴጂውን የማዘጋጀት ሂደቱ የተለያዩ የማሻሻያና የግብዓት ማሰባሰብ ሂደቶችን ያለፈ ሲሆን የዛሬው የመጨረሻ እንደሆነ ተነግሮለታል።
“የአዲስ አበባ ከተማ ደን ስትራቴጂ” ከ2019 ዓ.ም እስከ 2029 ዓ.ም ቆይታ አንደሚኖረው በመድረኩ ተገልጿል ።
በመቅደስ ደምስ