እስካሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የመራጭነት ካርድ ወስደዋል – ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

You are currently viewing እስካሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የመራጭነት ካርድ ወስደዋል – ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

AMN መጋቢት 20/2018 ዓ.ም

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በድምሩ 28 ሚሊዮን 365 ሺህ 310 መራጮች መመዝገባቸውን ገልጿል።

ከተመዝጋቢዎቹ መካከል 15 ሚሊዮን 317 ሺህ 567ቱ ወንዶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 13 ሚሊዮን 47 ሺህ 743ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል።

በሌላ በኩል፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳቸውን ለሕዝብ እንዲያስተዋውቁ ለማስቻል በሕዝብና በንግድ መገናኛ ብዙኃን ላይ የነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ ድልድል መደረጉን ቦርዱ አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review