የኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ሥርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

You are currently viewing የኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ሥርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

AMN- ግንቦት 6/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ዘገየ አስፋው ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በሥርዓተ ቀብሩ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በተለያዩ የመንግሥት የኃላፊነት እርከኖችና በሰብዓዊ አገልግሎት ዘርፍ ሀገራቸውን በታማኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ መሆናቸውን የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በተለይም በኢትዮጵያ ታሪክ ቀዳሚ ስፍራ የሚሰጠው የ”መሬት ለአራሹ” አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆንና የአርሶ አደሩ የመሬት ይዞታ መብት እንዲከበር ግንባር ቀደም ሚና ከተጫወቱ ቁልፍ ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review