የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪ ሚስተር ኦዌ ሳዳማሳ የመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከልን ጎበኙ

You are currently viewing የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪ ሚስተር ኦዌ ሳዳማሳ የመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከልን ጎበኙ

AMN ሚያዚያ 01/ 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያና የጃፓን ወዳጅነት ረጅም እድሜ ያስቆጠረ መሆኑን የሚታወቅ እና ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ያላት ተሳትፎ አለም የመሰከረላት እንደሆነ ለሚስተር ኦዌ ሳዳማሳ አጭር መብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡

በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የአለም አቀፍ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሚሰጡትን የግንባታ ስልጠናዎች ከሀገር ውስጥ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የማስተርስ ትምህርት እና አጫጭር ስልጠናዎች በማዕከሉ የሚሰጥ መሆኑ ተብራርቶላቸዋል፡፡

የመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ የጃፓን መንግስት ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ግዳጅ ተሳትፎ ለማጠናከር በሚሰሩ የአቅም ግንባታ ስራዎች በቋሚነት እየደገፈች መሆኗን አንስተው ለዚህም በማዕከሉ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይነትም በሶማሊያ AUSSOM የሰላም ማስከበር ተልእኮ ከአልሸባብ ተለዋዋጭ ባህሪና ታክቲክ አንፃር በሚሽኑ እያጋጠሙ በሚገኙ ተግዳሮቶች ለመፍታት ድጋፋቸዉን እንዲያጠናክሩና በስልጠናዎች፣ የማቴሪያልና የቴክኖሎጂ ትብብሮች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆኑና በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪ ሚስተር ኦዌ ሳዳማሳ በተደረገላቸው አቀባበልና ለቀጣይ በተቀመጠው ራዕይ መደሰታቸውን ገልፀው ኢትዮጵያ በሠላም ማስከበር ተሳትፎ ያላትን የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚያደንቁና በአቅም ግንባታ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሚስተር ኦዌ ሳዳማሳ መግለጻቸዉን ከሃገር መከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review