የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በህንድ የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው

You are currently viewing የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በህንድ የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው

AMN ግንቦት 6/2018 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር ) እ.ኤ.አ. ከሜይ 14 እስከ 15 ቀን 2026 በህንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ (BRICS) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ስብሰባው በህንድ ሰብሳቢነት “ፅናት፣ ፈጠራ፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር ሁሉንም ሀገራት በፍትሃዊነት የሚያገለግል ዓለም አቀፍ ስርዓት ለመገንባት የተቀናጀ የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተውበታል።

አሁን ያለው ዓለም አቀፋዊ ቀውስ በአስቸኳይ ካልተፈታ በሀገራት ድንበር ብቻ ሊገታ የማይችል ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ የፋይናንስ እና የማህበራዊ አለመረጋጋት መዘዞችን እንደሚያስከትልም አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም ብሪክስ ለሰላም መረጋገጥ እንዲሁም ለፍትሃዊ እና የተረጋጋ ዓለም አቀፍ ስርዓት ምሰሶ ለሆኑት ለጋራ ደህንነት እና ልማት ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንዳለበት አሳስበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review