AMN- ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬን ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ ዛሬ ከቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይት አድርጌያለሁ ብለዋል።
በቆይታቸው ወቅት በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለሙ በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ ማከናወናቸውን ነው የጠቀሱት፡፡

እነዚህ ውይይቶች እና የተፈረሙት ስምምነቶች ለሁለቱም ሀገራት የበለጸገ እና የተባበረ መጻኢ ዕድልን የሚያረጋግጡ፣ የቆዩ ግንኙነቶቻችንን ወደ ተጨባጭ ትብብር ለመቀየር እንደ ወሳኝ መሠረት የሚያገለግሉ የጋራ ቁርጠኝነታችን ማሳያ ጭምር ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገልጸዋል።