AMN-ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮችን ግንዛቤ በማስፋት ረገድ ሰፊ የሚዲያ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ ተናግረዋል።
ተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸምሙን የተቋሙ ማኔጅመንት አባላት እና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል፡፡
ተቋሙ ባለፉት 9 ወራት በስትራቴጂክ ግቦች አፈፃፀም ረገድ የነበሩ መልካም አፈፃፀሞችን፣ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን በስፋት ገምግሟል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሜትሮፖሊቲያን ሚዲያ እሳቤ በመቃኘት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እና ተደራሽ ለመሆን የጀመራቸውን የለውጥ (ሪፎርም) ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ሰለሞን ዲባባ ገልጸዋል፡፡

በተለይም ተቋሙ የፊታችን ግንቦት ወር ላይ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ትኩረት በመስጠት የመራጮችን ግንዛቤ በማስፋት ረገድ ሰፊ የሚዲያ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ ይሄው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በሚካኤል ሂሩይ