የአዲስ አበባ ኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማት ስራዎች እድገት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተናበበ መልኩ እንደሚከወን ማሳያ ናቸው – አሕመድ ሺዴ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማት ስራዎች እድገት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተናበበ መልኩ እንደሚከወን ማሳያ ናቸው – አሕመድ ሺዴ

AMN – ሚያዝያ 19 /2018 ዓ/ም

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ላይ ማዕከል ያደረገ ውጤታማ የልማት አቅጣጫ ላይ ናት ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ገለጹ።

የአየር ንብረት ኢንቨስትመንት ፈንድስ ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የልምድ ልውውጥ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ላይ ምሁራን፣ የልማት አጋሮችና ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ጨምሮ አምባሳደሮችና የሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል።

ለሶሰት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ የተለያዩ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ያገኟቸው ውጤቶች ላይ ተሞክሮዎችን አቅርበው የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

አቶ አሕመድ ሺዴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷የኢትዮጵያ የዕድገት ራዕይና አቅጣጫ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ላይ ማዕከል ያደረገ ነው።

ለዚህም ታዳሽ ሃይልን ማስፋፋት፣የውሃ አቅርቦት ማሻሻል፣የተራቆቱ መሬቶች መልሰው እንዲያግሙ በማድረግ የማህበረሰቡን የመቋቋም አቅም የሚያሳድጉ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳር ልማት ስራዎች ከተማዋን ዘመናዊ ከማድረጋቸውም ባሻገር እድገት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተናበበ መልኩ እንዴት እንደሚከወን ማሳያ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአየር ንብረት ኢንቨስትመንት ፈንድስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ታሪዬ ባድጌሲን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል በአረንጓዴ አሻራ አርዓያ የሚሆን ተግባር መፈጸሟን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከዚህ ቀደም ስኬታማ በሆነ መንገድ ማስተናገዷም በዘርፉ ያላትን የላቀ ተሞክሮ ያሳያል ብለዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድስ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጋራ የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review