ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም
ለሁለት ወራት የዘለቀው የአሜሪካና የኢራን ጦርነት አሁንም መቋጫ አላገኘም፡፡
ይህንኑ ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ እሁድ እለት ወደ ፓኪስታን እና ኦማን ካደረጉት የሽምግልና ጉዞ በኋላ ወደ ሩሲያ አቅንተዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ድርድር የምትፈልግ ከሆነ በስልክ ልታገኘን ትችላለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ትራምፕ ይህንን ያሉት የቴህራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ድጋፍ ለማግኘት ሰኞ እለት ሞስኮ በገቡበት ወቅት ነው።
የዶናልድ ትራምፕ ልዑካኖች ወደ ኢስላማባድ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ መሰረዙን ተከትሎ የሰላም ተስፋው ተሟጥጧል።
ሁለቱ ወገኖች በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር እና በሆርሙዝ የባህር ስርጥ በኩል በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ አሁንም ድረስ መግባባት አልቻሉም፡፡
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ለሁለተኛ ዙር ታቅዶ የነበረው የሰላም ንግግር ዳግም መስተጓጎሉን ተከትሎ የዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በ2 በመቶ ገደማ መጨመሩን ቢቢሲ ዘግቧል።
የኢራን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ወሳኝ የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ በግጭቱ ምክንያት በመዘጋቱ የዓለም የኢነርጂ አቅርቦት ከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቋል።
አንዳንድ የስትራቴጂ ባለሙያዎች መስመሩ ለተጨማሪ ጥቂት ሳምንታት ተዘግቶ የሚቆይ ከሆነ ውጤቱ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ እጅግ ሰፊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በወንድምአገኝ አሰፋ