AMN-ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም
ኢትዮጵያውያን ብስክሌተኞች የሚሳተፉበት “የአረንጓዴው መንገድ” የሚል ስያሜ የተሰጠው የብስክሌት ውድድር መነሻውን ቦሌ አትላስ አድርጎ ጀምሯል።
የውድድሩ የክብር እንግዳ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መክዩ ሞሃመድ ውድድሩን በይፋ አስጀምረዋል።
ክልል የተገኙ ፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር የመጡ ክለቦች እንዲሁም መቀመጫቸውን ውጪ ሀገራት ያደረጉ ብስክሌተኞች እየተወዳደሩ ይገኛሉ።
ከዚህ ውጪ የብስክሌት ስፖርት በሀገሪቱ እንዲዘወተር በማሰብ በመቶዎች የሚቀጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በሁለቱም ፆታ ከ150 በላይ ፕሮፌሽናል ብስክሌተኞች በሚሳተፉበት ውድድር ላይ ከ1-10 የሚወጡት ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል። ውድድሩ 90 ኪ.ሜ የሚፈጅ ይሆናል።
ውድድሩ ነገ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የዓለም አቀፍ ሲቲ ማውንቴን ውድድር ማጀቢያ እንዲሆን ታስቦ እንደተዘጋጀም ተገልጿል።
በሸዋንግዛዉ ግርማ