የከተማ አስተዳደሩ የመስሪያ ቦታዎችን በማልማትና ፍትሃዊ በመሆነ መንገድ በማስተላለፍ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ ይገኛል – ወ/ሮ አይዳ አወል

You are currently viewing የከተማ አስተዳደሩ የመስሪያ ቦታዎችን በማልማትና ፍትሃዊ በመሆነ መንገድ በማስተላለፍ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ ይገኛል – ወ/ሮ አይዳ አወል

AMN – ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም

የከተማ አስተዳደሩ የመስሪያ ቦታዎችን በማልማትና ፍትሃዊ በመሆነ መንገድ በማስተላለፍ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማት እና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይዳ አወል ገለጹ፡፡

ዳይሬክተሯ ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢንተርፕራይዞችና ለአንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ሼዶችን ባስተላለፈበት ወቅት ነው፡፡ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗን ገልጸው፤ ይህንኑ ደረጃ የሚመጥን ስራ በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አክለውም ኤጀንሲው በከተማ አስተዳደሩ ከተመረጡ 16 የሪፎርም ተቋማት አንዱ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ ማዘመን፤ የመስሪያ ቦታዎችን ማልማትና በፍትሃዊነት ማስተላለፍ፤ እንዲሁም ግልጽነት ያለው የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን አብራርተዋል።

መንግስት ሰው ተኮር በመሆኑ የዜጎች ህይወት ሲቀየር ሀገር ትቀየራለች ብሎ ያምናል ያሉት ወ/ሮ አይዳ፤ በተለይም ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ከስደት ተመላሾች በስራ እንዲሰማሩ የመስሪያ ቦታ ማመቻቸት የኢኮኖሚና ማህበራዊ መረጋጋት ቁልፍ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

በዛሬው ዕለት ቁልፍ የተረከቡት ኢንተርፕራይዞች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ግልጽ በሆነ የዕጣ አወጣጥ ስርዓት የተመረጡ መሆናቸውን በመግለጽ፤ ይህም አስተዳደሩ ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር እያከናወነ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review