በመራጭ ተመራጭ ከህዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ አቅርበናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በመራጭ ተመራጭ ከህዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ አቅርበናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN — ሚያዚያ 30 / 2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፤ ዛሬ 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በመራጭ ተመራጭ ከህዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ አቅርበናል ሲሉ አስታወቁ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ ከቤት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ፍላጐትና አቅርበትን ለማጣጣም 5 ስትራተጂዎችን ነድፈን በመንግሥት በጀት፣ በመንግስትና በግል አጋርነት፣ በግል፣ በሪልስቴት እና በግለሰብና ግለሰብ ቤቶችን እየገነባን እንገኛለን ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ በመንግሥት በጀት 50 ሺህ ቤቶችን፤ በመንግሥትና የግል አጋርነት 55 ሺህ በአጠቃላይ 105 ሺህ ቤቶች እየተገነቡ ነው ። አሁን ላይ አፈፃፀማቸው ከ40 እስከ 90% እየተጠናቀቁ ነው። በመንግስት የሚገነቡት ሲጠናቅቁ ቅድሚያ ስጥተን እየቆጠቡ ላሉት የሚተላለፉ ይሆናል ሲሉ ጠቁመዋል።

የኑሮ ውድነት ዓለም አቀፍ ክስተት መሆኑ ይታወቃል ያሉት ከንቲባ አዳነች ሆኖም በገበያ ማዛባት የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ የቁጥጥር ሥርዓተ መዘርጋት፥ የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ በብዛትና በጥራት ማምረት፥ ተኪ ምርቶችና ማምረት ፥ በአምስት መግቢያ በሮች ስድስት የገበያ ማዕከላትን የእሁድ ገበያዎችን በተለያዩ የከተማው ቦታዎች መስርተን ለነዋሪዎች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ችለናል ብለዋል።

በተጨማሪም 18 ቢሊዮን ብር ድጎማ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ድጎማ በማድረግ የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ሰርተናል ያሉት ከንቲባ አዳነች አዲስ አበባን የጤና ቱሪዚም ማዕከል ለማድረግ በሰራናቸው ሥራዎች 4 አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተዋል።

እንዲሁም 9 በመጀመሪያ ሆስፒታል ደረጃ የተገነቡ ጤና ጣቢያዎች ተገንብተዋል። አብዛኛዎቹን ነባሮቹ ሆስፒታሎችን ዘመናዊ፣ ቴክኖሎጂ የተሟላላቸው እና በአልጋ ቁጥርም በእጥፍ እንዲጨምሩ አድርገን አድሰናቸዋል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የትራንስፓርት አግልግሎት ለማሻሻል በዋናነት የመንገድ መሰረተ ልማቱን የማስፋት ስራ ሰርተናል ያሉ ሲሆን የመኪና፥ የብስክሌት እና የእግረኛ መንገዶችን ተለይተው ተገንብተዋል ። የመንገድ ሽፋንን 12.8% ወደ 20.% አሳድገናል። 163000 መኪናዎችን ማቆም የሚችሉ ፓርኪንግ ገንብተናል ሲሉ ለምክር ቤት አባላት አብራርተዋል።

በከተማችን ለህጻናት ምቹ የሚጫወቱባቸው ከ5ሺህ በላይ የልጆች መጫወቻ ፣እንክብካቤ የሚያገኙበት ከ1000 በላይ ዴይ ኬር ገንብተን ወደ ስራ አስገብተናል ያሉት ከንቲባ አዳነች ወጣቶች በአእምሮና በአካል የዳበረ እንዲሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያዎች በየሰፈሩ ገንብተናል፥ ትላልቅ ስታዲየሞችም እየተገነቡ መሆኑን ገልጸዋል ።

ወጣቶቹን ተወዳዳ ብቁ ለማድረግም በኢኒሼቲቭ ከ3000 በላይ ወጣቶች ላይ ልዩ ስልጠና እየሰጠን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ከነጠላ ትርክት ይልቅ አሰባሳቢ ትርክትን ለመፍጠር ለኪነጥበብ ስራዎች መከወኛዎች በስፋት ገንብተናል። በዘርፋም የሰው ሃይል ለማብቃት አሁንም አቅደን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል።

74 በመቶ የሚሆነውን የከተማችንን ጎስቋላ ገጽታ ለመቀየር ወደ ውብ ምቹ ከተማ ለማድረግ በሰራነው ሥራ ወደ 30 በመቶ ማድረስ ችለናል። ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን ለማስተካከል ሰፋፊ የፍሳሽ መስመሮችን ገንብተናል፤ የነበሩትንም አስፋፍተናል። በዚህም በቀሻሻ አወጋገድ ስርዓት ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት ችለናል ብለዋል ከንቲባ አዳነች ።

በከተማችን መብራት ለማስፋፋት በተሰራው ስራ ጨለማ የነበሩ አካባቢዎች ተገልጠዋል፤ በዚህም ለወንጀል አጋላጭ የነበሩ አካባቢዎች ተቀይረዋል። የትራፊክ አደጋንም በዚሁ ልክ መቀነስ ችለናል። በቀሩ አካባቢዎችም አቅደን በስፋት የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።

በተግዳሮት ውስጥ የነበረው አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን በስድስት ማዕከላት ተግባራዊ ማድረግ ችለናል። በዚህም 150 አገልግሎቶች ወደ መሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከል በማስገባት ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል። በአጭር ጊዜ ውስጥም ቀሪ አምስት ማዕከላት ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ሙስናና ለአገልግሎት እጅ መንሻ የሚጠይቁትን ለማጋለጥ ፥ በሚዲያ በግልፅ ተጠያቂ የማድረግ፤ አስተዳደራዊና በወንጀል በህግ ተጠያቂነትን የማስፈን ስራዎች እየሰራን ነው። እስከ 9ወር ድረስ ባለው የተያዙ ተጠርጣሪዎች 420 ሲሆን፥ አመራር 40፥ ባለሙያ 230፥ የተጠረጠሩበት ወንጀል ተጠቀሚ ሰዎች 150 ሲሆኑ ሁሉንም እንደየተሳትፎቸዉ ተጠያቂ ተደርገዋል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review