AMN – ግንቦት – 1/2018 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የተመረጡትን የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌን የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ለመታደም ዛሬ ጅቡቲ ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስፍራው በመገኘት ለፕሬዚዳንቱ ያላቸውን ልባዊ ደስታና መልካም ምኞት ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለሀገራቸው የሚሰጡት አገልግሎት የጅቡቲን ሁለንተናዊ እድገት አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

አክለውም በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል ያለው ታሪካዊ ወዳጅነትና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት አረጋግጠዋል።
ይህ የሁለቱ ሀገራት የቆየ ጥብቅ ግንኙነት ለሕዝቦቻቸው የጋራ ብልጽግና ከሚኖረው ፋይዳ ባለፈ፣ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት መጠናከር እንደ አንድ ትልቅ መሠረት እንደሚወሰድም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።