AMN- ግንቦት 4/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጀግናዋ የረጅም ርቀት አትሌት የብርጓል መለሰ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሐዘን ገለጸ።
አትሌት የብርጓል መለሰ በመደበኛ ልምምድዋ ላይ እያለች ነው በድንገት ሕይወቷ ማለፉ የተገለጸው።
አትሌት የብርጓል በተለያዩ ውድድሮች ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈች ሲሆን እ.ኤ.አ በ2015 በኮንጎ ብራዛቪል በተካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ሀገሯን ወክላ በግማሽ ማራቶን ውድድር የነሃስ ሜዳልያ አሸንፋለች ።
በ2015ቱ የቺካጎ ማራቶን የብር ሜዳሊያ ባለቤት፤ የሻንጋይ፣ ፕራግ እና ሁውስተን ማራቶኖች አሸናፊ ፣ የፓሪስ ግማሽ ማራቶን (ሁለት ጊዜ) እና የሊዝበን ግማሽ ማራቶን አሸናፊ በመሆን ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ስታስጠራ እንደነበር ፌደሬሽኑ ባወጣው የሐዘን መግለጫ አመልክቷል።
በካናዳ በሚካሄደው የኦታዋ ማራቶን ለመሳተፍ ዝግጅት ስታደርግ እንደነበር ነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጠቀሰው።
ፌዴሬሽኑ ባወጣው የሐዘን መግለጫ ፣ በጀግናዋ አትሌት ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን መራር ሀዘን በመግለፅ ለቤቸሰቦችው ፣ ወዳጆችዋ ፣ አድናቂዎቻቸው እና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።