7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የነዋሪዎች ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የነዋሪዎች ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

AMN – ግንቦት 13/2018 ዓ.ም

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች የተለመደ ንቁ ተሳትፏቸውን እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጥሪ አቀረበ።

ቢሮው ምርጫን ተከትሎ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል፣ በመቆጣጠር እና ሰላማዊ የምርጫ ሂደት እንዲኖር በማድረግ ረገድ ያለውን የሕዝብ ሚና በተመለከተ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ፣ የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ተቀናጅተው ሊፈጥሩ የሚችሉትን የወንጀል ሴራ ቀድሞ በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ከምንጊዜውም በላይ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።

ኃላፊዋ አክለውም፣ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ የሆነው ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ በከተማዋ ያለውን አስተማማኝና የጸና ሰላም ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት በከተማዋ ለተመዘገቡት ሁለንተናዊ ስኬቶች የነዋሪዎች አስተዋጽኦ የማይተካ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ሊዲያ ፣ በመጪው የምርጫ ወቅትም ነዋሪዎች የጸጥታ አካላትን በመደገፍ የተለመደ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review