AMN ግንቦት 18/2018
የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የብልጽግና ፓርቲ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅስቀሳ መርሀ ግብርና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ከማለዳው ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ ከጌዴኦ ዞንና ከዲላ ከተማ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

በሰልፉም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌታዊ ሀገር እናሻግር የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛል።